Art & Culture

 • አስገራሚው ልጅ.. An Amazing Boy

  አስገራሚው ልጅ......
  .
  የማወራችሁ ውሸት አይደለም ልብወለድም
  እንዳይመስላችሁ...
  ህፃን ሀይለአምላክ አክሊሉ ይባላል .... የተወለደው አዲስ አበባ ሲሆን አሁን 9ኛ አመቱን ይዟል።
  የ 3ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ሲያድግ ተምሮ መሆን የሚመኘው ነገር በሙሉ ከሁሉም ህፃናት ተማሪዎች የተለየ ነው።
  ሀይለአምላክ ገና በእዚህ እድሜው ሳንቲም
  መለቃቀም ይወዳል። የቤተሰቦቹን ጫማ በሙሉ ያፀዳና አንድ አንድ ብር ይቀበላቸዋል። ቤተሰቦቹ
  ጫማቸውን ሌላ ቦታ ለሊስትሮ አስጠርገው ከመጡ እሪ ብሎ ያለቅሳል። ሀይለአምላክ በእዚህ እድሜው ሳንቲም የመለቃቀሙ ነገር ቤተሰቦቹን አስጨንቋቸዋል። የሚሰጠውን ፍራንክ ምን እንደሚገዛበት የት እንደሚያደርሰው ፈፅሞ አይታወቅም። ብቻ አምስት ሳንቲም ትሁን አስር ሳንቲም ይቀፍላል! ... ይሄ ገና ሳያድግ ቅፈላ የለመደው ልጃቸው ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ቆንጥጠውታል፣ገርፈውታል።
  ነገር ግን ህፃን ሀይለአምላክ ይሄን ባህሪውን የሚተው ልጅ አይደለም እንደውም ይባስ ብሎ እያለቀሰ እና እንባውን እያዘራ
  "የተመታሁበትን አንድ ብር ስጡኝ"ይላል።
  ቤተሰቦቹም መልሰው ፈገግ ይሉና እንባውን
  እየጠራረጉለት ቤተሰባዊ ፍቅር ይሰጡታል።
  ያች የለመዳት አንድ ብር ትሰጠዋለች ያችን ይዞ ልቅሶውን አቁሞ ወደ ውጭ ይሮጣል.... ምን እንደሚገዛበት አይታወቅም።
  .
  ሀይለአምላክ ሁሌ ከወንድሙ ክፍል እየገባ
  ሞባይል መነካካትም ይወዳል ሁሌ የሚያየው ግን ተመሳሳይ ፎቶ ብቻ ነው። ይሄን ፎቶ እድሜ ለወንድሙ እንጂ በሀካልም አይቶታል እዚህ
  ፎቶ ለይ ያሉ ሰዎች ግን በእድሜ የገፉ
  መንገድ ለይ ወድቀው አይዞአችሁ የሚላቸው ያጡ፣አካላቸው ጎሎ መስራት ሳይችሉ
  ቀርተው እራብ የሚጫወትባቸው፣አስታማሚ
  አጥተው ራቁታቸውን ሜዳ ለይ ወድቀው ማህበረሰቡ እብድ ይላቸው የነበሩ የአእምሮ ህሙማኖችን ፎቶ ነበር የሚያየው።
  እነዚህን ሁሉ ፎቶዎች ሁሌ እያየም በህፃንነት አንደበቱ ልደግ ብቻ ይላል።
  .
  ለሀይለአምላክ እንደዚህ መሆን ሚስጥሩ አንድ እና አንድ ወንድሙ ነው። ወንድሙ ከሁለት ወር በፊት ሽሮሜዳ ወደ ሚገኘው "የወደቁትን አንሱ የአረጋዊያን መርጃ ማእከል" ይዞት ሄዶ ነበር።
  ይሄን ድንቡሼ ህፃን በማእከሉ ውስጥ ተረጂ አረጋዊያን በጣም ሲስሙት እና ህፃናዊ ፍቅር ሲሰጡት ነበር ያች ፍቅር አምሮው ውስጥ ቀርታለች።
  .
  ዛሬ ግን ለእኒህ ሰዎች እሱም የበኩሉን
  አስተዋፅኦ ሊያደርግ ነው። ወንድሙ ከእኔ ጋር እሁድ አረጋዊያኑን ምሳ እንደምናበላ በስልክ
  ስናወራ ሰምቶ ኖሯል።
  "አቤል እኔም ላብላ"ብሎ በተኮላተፈ ህፃናዊ
  አንደበቱ ተናገረ።
  አቤል አንቺ ስታድጊ ታበያለሽ እሺ ብሎ
  መለሰለት ! ይሄ ህፃን ግን ማድረግ እንደሚችል ስላመነ ወደ ውጭ ወጥቶ በተደራረቡ ጥቋቁር ፔስታሎች የታሰረ ነገር ይዞ መጣ እና እምብዬው ፍራንክ አለኝ አበላለሁ ብሎ አለቀሰ።
  አቤልም የመጣውን ፔስታል ሲፈታ ብዙ ሳንቲሞች እና የተወሰኑ አንድ አንድ ብሮች ናቸው ሲቆጠር
  154.35 ሳንቲም ሆነ ... መላ ቤተሰቡ በአግርሞት ጭንቅላቱን ያዘ።
  ማንም ትልቅ ሰው ያላሰበውን ጭንቅላት ይሄ ቲኒሽዬ ልጅ በቲኒሽዬ ጭንቅላቱ ትልቅ ነገር
  አስቦባታል።
  እነዚያን አንድ ቀን ያያቸውን አረጋዊያን ብር ሰብስቦ ለመርዳት የቤተሰቦቹን ጫማ አጥቧል፣አምስትም
  አስርም አጠራቅሟል።
  የእሱ ትምህርት ሲጨርስ እና ሲያድግ ምኞት እነ እማማን እና እነ አባባን እንጀራ ማብላት ነው ይላል!
  ለካ እማማ እና አባባ ለእሱ የተራቡቱ ናቸው።
  .
  የምር ይሄን አንድ ፍሬ ልጅ ድርጊቱን ቀናሁበት
  ለካ እየተገረፉ እና እየተቆነጠጡም መልካም መሆን ይቻላል!

  Weynafera Yohannes fb page

  Read more
 • ከ 50,000 በላይ የኢትዮጵያ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት በውጭ ሀገር ይገኛሉ! / More than 50,000 Ethiopian manuscripts are available abroad

  ከ 50,000 በላይ የኢትዮጵያ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት በውጭ ሀገር ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ ከ11,000 በላይ የሚሆኑት በማይክሮ ፊልም ተነስተዋል (digitalized ሆነዋል)። የሄዱት በዘረፋ ነው። (አሁንም ዘረፋው አልቆመም)።
  ከእነዚህ መጻሕፍትም አብዛኞቹ የፍልስፍና፣ የህክምና፣ የሥነ ምግባርና ሥነ ልቦና፣ የሥነ ከዋክብትና (ህዋ ሳይንስ)፣ የሥነ ዕጽዋት፣ የአዕዋፍና እንስሳት ምርምር ውጤቶች ናቸው።
  ለምሳሌ ጀርመን ውስጥ በኢትዮጵያ ብራና መጻሕፍት ብቻ ተመራምረው ያቋቋሟቸው መድኃኒት ፋብሪካዎች አሉ።
  በሀገራቸው ዩኒቨርሲቲዎች የግዕዝ ቋንቋን እስከ PhD ድረስ የሚያስተምሩበት ምሥጢርም ይኸው ነው።በተለይ ምዕራባውያን በትልልቅ ሙዝየሞቻቸው ውስጥ በክብር ካስቀመጧቸው ውድ ሀብቶቻቸው ውስጥ የእኛ ብራና መጽሐፎች ይገኙበታል። በግልጽ እየተጎበኙ ገቢ ከማስገኘታቸውም በላይ ለምርምር ሥራ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
  የእኛ ብራናዎች የማይገኙበት ሀገር አለ ለማለትም ይከብዳል። አብዛኛዎቹ ግን አውሮፓ ውስጥ ናቸው። በቫቲካን (ጣሊያን ውስጥ) 1,082
  በፈረንሳይ 1,034
  በእንግሊዝ 850
  በአየርላንድ 66
  በጀርመን 820
  በስዊድን 88
  በሰሜን አሜሪካ 400 የብራና መጻሕፍት በሙዝየሞችና በቤተ መጻሕፍት ውስጥ በግልጽ ተመዝግበውና ካታሎግ ተሠርቶላቸው ይገኛሉ። (እነዚህ ለምሳሌ የቀረቡ ናቸው)።
  ከታሰበበትና ከተሠራበት እነዚህንም ሆነ ሌሎች ቅርሶችን የማስመለስ መብቱ አለን። የእኛ መሆናቸው በግልጽ የተመዘገበና የታወቀ ስለሆነ።
  (የአክሱም ሐውልትና የላሊበላው አፍሮ አይገባ መስቀ ል መመለሳቸውን ልብ እንበል… ከተሠራ የራሳችንን ቅርስ የማስመለስ መብታችን የተጠበቀ ነው)። ግን እኛ ይህ ጉዳያችን የሆነ አይመስልም። በተለይ አቅሙና እውቅናው ያለን አካላት… ከቤተ ክህነቱ ጀምሮ ዝም ብለናል።
  የሚገርመው ደግሞ እኛ ዝም ብንልም አንዳንድ ቅን የሆኑ የውጭ ምሁራን ዝም አላሉም። ለምሳሌ ፕሮፌሰር ስቲቭ የተባሉ ተመራማሪ ብቻ ከ400 በላይ የብራና መጻሕፍቶቻችንን በማይክሮ ፊልም አንስተው በዌብሳይት ጭነው ለዓለም ሁሉ እያስተዋወቁና “የኢትዮጵያ መሆናቸውን” እየተናገሩ ነው።በጣም የሚያሳዝነው ግን አሁንም ዘረፋው አለመቆሙ ነው። በውድ ገንዘብ ስለሚሸጡ (በሚሊየን ብሮች) እንቅስቃሴውን ማስቆም ከባድ ሆኖአል። እንዲያውም የትልልቅ ገዳማት አባቶች ታማኞችና ከገንዘብ ፍላጎት የራቁ መሆናቸው እንጅ እስካሁን ተዘርፈው ያልቁ ነበር። እስኪ ስለዚህ ጉዳይ እንነጋገር። የእኛን ብራናዎች በሚሊየን ብሮች የሚገዙት ውጮች ለምን ይመስላችኋል? ትልቅ ምሥጢራዊ ሀብት የያዙ ባይሆኑ እንዲህ ተፈላጊ ይሆኑ ነበርን? የእኛን ወርቆች በብር እየሸጥን የእነርሱን መዳብ በወርቅ እየገዛን ነው። የእኛ መጻሕፍት ለሥልጣኔያቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ባይኖራቸው ኖሮ በአሳሽነትም በሃይማኖት ሰባኪነትም ሲያሻቸውም እንደ እንግሊዝና ጣሊያ በጦርነት ስም እየመጡ ባልዘረፉን ነበር።
  ጀምስ ብሩስ የዓባይን ምንጭ ለማግኘት በሚል ሰበብ ጎንደር ድረስ ሄዶ፣ ጎጃምና ወሎንም ሸዋንም አስሶ ወደ ዝዋይም ወርዶ ከቤተመንግሥቱ ቤተ መጻሕፍትም ከገዳማትም መጽሐፈ ሄኖክን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋቸውም እጅግ ከፍ ያለ መጻሕፍትን በምሥጢር አግዞ ወሰደ።
  እንግሊዞች አፄ ቴዎድሮስን ለመውጋት መጥተው መቅደላ ላይ የነበረውን ታላቅ የብራና መጻሕፍት ቤተ መዘክር ዘርፈው በብዙ ሺህ መጻሕፍትን ወሰዱ። ጣሊያኖች በሁለቱም ጦርነቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ብራና መጻሕፍትን ዘረፉ።
  ሌሎች በሃይማኖት “ሚሽን” አሳበው ብዙዎችን ሰረቁ… ለምን? የእኛ መጻሕፍት የያዙት እውቀት ጥልቅነትና የሥልጣኔ ምሥጢርነት ቢገባቸው ነው)።

  More than 50,000 Ethiopian manuscripts are available abroad

   

  Read more

Latest Articles

Most Popular

google.com, pub-5833971792216939, DIRECT, f08c47fec0942fa0