9 ወራት ውስጥ 538 የበይነ መረብ ጥቃቶች / There have been 538 internet attacks in the last 9 months

ባለፉት 9 ወራት 538 የበይነ መረብ ጥቃቶች ደርሰዋል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012

         በኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ 538 የበይነ መረብ ጥቃቶች መድረሳቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ከተፈጸሙት ጥቃቶች 263ቱ በአጥፊ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) የተፈጸሙ ጥቃቶች ሲሆኑ፣ 106 ወዳልተፈቀደ ሲስተም ሰርጎ መግባት፣ 105 የድረ ገፅ ጥቃቶች፣ 54 የመሰረተ ልማት ቅኝት፣ 9 የበይነ መረብ መሠረተ ልማቶችን ሥራ ማቋረጥ እንዲሁም 1 በበይነ መረብ ማጭበርበር መሆኑንም አስታውቋል።

በሃገሪቱ ባለፉት 9 ወራት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የበይነ መረብ ሳይበር ጥቃት 48 ነጥብ 9 በመቶው የሚሆኑት አጥፊ ሶፍትዌሮችን (ማልዌር) በመጠቀም የተፈጸሙ መሆኑን የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን /ኢትዮ-ሰርት/ ገልጿል።

ቁጥራቸው 106 የሚሆኑት ጥቃቶች ደግሞ ወዳልተፈቀደ ሲስተም ሰርጎ በመግባት የተፈጸሙ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ጥቃቶች 19 ነጥብ 7 ከመቶ ሲሆን፥ በድረ ገጽ ላይ የተከሰተው ጥቃት ደግሞ 105 ወይም 19 ነጥብ 5 ከመቶ በመያዝ ከማልዌር ጥቃት በመቀጠል ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል።

በተለየ ሁኔታ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ በከፍተኛ መጠን የተከሰተው የበይነ መረብ ጥቃት በማልዌሮች የተፈጸሙ ጥቃቶች መሆናቸውን የጠቆመው ኢትዮ ሰርት እነዚህ የማልዌር ጥቃቶች በተለያዩ መንገዶች የሚፈጸሙ ናቸው ብሏል።

ከቀደሙት ሁለት ሩብ ዓመት አንጸር በሶስተኛው ሩብ ዓመት የበይነ መረብ ጥቃቱ ጭማሪ ማሳየቱን የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን /ኢትዮ-ሰርት/ አስታውቋል፡፡

በዚህም በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የደረሰው የበይነ መረብ ጥቃት 113 ሲሆን በሁለተኛው ሩብ ዓመት ደግሞ 172 እንዲሁም በሶስተኛው ሩብ ዓመት ቁጥሩ 253 መድረሱን ዲቪዥኑ ገልጿል።

በያዝነው 2012 በጀት ዓመት ከሁለተኛው ሩብ ዓመት አንጻር በ3ኛው ሩብ ዓመት የጥቃት መጠኑ 68 በመቶ ከፍ ማለቱን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Source

Fana Broadcasting


There have been 538 internet attacks in the last 9 months Addis Ababa, April 24, 2012 (FBC) The Information Network Security Agency reported 538 cyber attacks in Ethiopia over the past nine months. The agency said 263 of the attacks were attacks by malicious software, 106 unauthorized hacking systems, 105 web attacks, 54 disruption of internet infrastructure, and 1 Internet fraud.

Related Articles

Latest Articles

Most Popular

google.com, pub-5833971792216939, DIRECT, f08c47fec0942fa0