Welcome
Login / Register

አስገራሚው ልጅ.. An Amazing Boy

አስገራሚው ልጅ......
.
የማወራችሁ ውሸት አይደለም ልብወለድም
እንዳይመስላችሁ...
ህፃን ሀይለአምላክ አክሊሉ ይባላል .... የተወለደው አዲስ አበባ ሲሆን አሁን 9ኛ አመቱን ይዟል።
የ 3ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ሲያድግ ተምሮ መሆን የሚመኘው ነገር በሙሉ ከሁሉም ህፃናት ተማሪዎች የተለየ ነው።
ሀይለአምላክ ገና በእዚህ እድሜው ሳንቲም
መለቃቀም ይወዳል። የቤተሰቦቹን ጫማ በሙሉ ያፀዳና አንድ አንድ ብር ይቀበላቸዋል። ቤተሰቦቹ
ጫማቸውን ሌላ ቦታ ለሊስትሮ አስጠርገው ከመጡ እሪ ብሎ ያለቅሳል። ሀይለአምላክ በእዚህ እድሜው ሳንቲም የመለቃቀሙ ነገር ቤተሰቦቹን አስጨንቋቸዋል። የሚሰጠውን ፍራንክ ምን እንደሚገዛበት የት እንደሚያደርሰው ፈፅሞ አይታወቅም። ብቻ አምስት ሳንቲም ትሁን አስር ሳንቲም ይቀፍላል! ... ይሄ ገና ሳያድግ ቅፈላ የለመደው ልጃቸው ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ቆንጥጠውታል፣ገርፈውታል።
ነገር ግን ህፃን ሀይለአምላክ ይሄን ባህሪውን የሚተው ልጅ አይደለም እንደውም ይባስ ብሎ እያለቀሰ እና እንባውን እያዘራ
"የተመታሁበትን አንድ ብር ስጡኝ"ይላል።
ቤተሰቦቹም መልሰው ፈገግ ይሉና እንባውን
እየጠራረጉለት ቤተሰባዊ ፍቅር ይሰጡታል።
ያች የለመዳት አንድ ብር ትሰጠዋለች ያችን ይዞ ልቅሶውን አቁሞ ወደ ውጭ ይሮጣል.... ምን እንደሚገዛበት አይታወቅም።
.
ሀይለአምላክ ሁሌ ከወንድሙ ክፍል እየገባ
ሞባይል መነካካትም ይወዳል ሁሌ የሚያየው ግን ተመሳሳይ ፎቶ ብቻ ነው። ይሄን ፎቶ እድሜ ለወንድሙ እንጂ በሀካልም አይቶታል እዚህ
ፎቶ ለይ ያሉ ሰዎች ግን በእድሜ የገፉ
መንገድ ለይ ወድቀው አይዞአችሁ የሚላቸው ያጡ፣አካላቸው ጎሎ መስራት ሳይችሉ
ቀርተው እራብ የሚጫወትባቸው፣አስታማሚ
አጥተው ራቁታቸውን ሜዳ ለይ ወድቀው ማህበረሰቡ እብድ ይላቸው የነበሩ የአእምሮ ህሙማኖችን ፎቶ ነበር የሚያየው።
እነዚህን ሁሉ ፎቶዎች ሁሌ እያየም በህፃንነት አንደበቱ ልደግ ብቻ ይላል።
.
ለሀይለአምላክ እንደዚህ መሆን ሚስጥሩ አንድ እና አንድ ወንድሙ ነው። ወንድሙ ከሁለት ወር በፊት ሽሮሜዳ ወደ ሚገኘው "የወደቁትን አንሱ የአረጋዊያን መርጃ ማእከል" ይዞት ሄዶ ነበር።
ይሄን ድንቡሼ ህፃን በማእከሉ ውስጥ ተረጂ አረጋዊያን በጣም ሲስሙት እና ህፃናዊ ፍቅር ሲሰጡት ነበር ያች ፍቅር አምሮው ውስጥ ቀርታለች።
.
ዛሬ ግን ለእኒህ ሰዎች እሱም የበኩሉን
አስተዋፅኦ ሊያደርግ ነው። ወንድሙ ከእኔ ጋር እሁድ አረጋዊያኑን ምሳ እንደምናበላ በስልክ
ስናወራ ሰምቶ ኖሯል።
"አቤል እኔም ላብላ"ብሎ በተኮላተፈ ህፃናዊ
አንደበቱ ተናገረ።
አቤል አንቺ ስታድጊ ታበያለሽ እሺ ብሎ
መለሰለት ! ይሄ ህፃን ግን ማድረግ እንደሚችል ስላመነ ወደ ውጭ ወጥቶ በተደራረቡ ጥቋቁር ፔስታሎች የታሰረ ነገር ይዞ መጣ እና እምብዬው ፍራንክ አለኝ አበላለሁ ብሎ አለቀሰ።
አቤልም የመጣውን ፔስታል ሲፈታ ብዙ ሳንቲሞች እና የተወሰኑ አንድ አንድ ብሮች ናቸው ሲቆጠር
154.35 ሳንቲም ሆነ ... መላ ቤተሰቡ በአግርሞት ጭንቅላቱን ያዘ።
ማንም ትልቅ ሰው ያላሰበውን ጭንቅላት ይሄ ቲኒሽዬ ልጅ በቲኒሽዬ ጭንቅላቱ ትልቅ ነገር
አስቦባታል።
እነዚያን አንድ ቀን ያያቸውን አረጋዊያን ብር ሰብስቦ ለመርዳት የቤተሰቦቹን ጫማ አጥቧል፣አምስትም
አስርም አጠራቅሟል።
የእሱ ትምህርት ሲጨርስ እና ሲያድግ ምኞት እነ እማማን እና እነ አባባን እንጀራ ማብላት ነው ይላል!
ለካ እማማ እና አባባ ለእሱ የተራቡቱ ናቸው።
.
የምር ይሄን አንድ ፍሬ ልጅ ድርጊቱን ቀናሁበት
ለካ እየተገረፉ እና እየተቆነጠጡም መልካም መሆን ይቻላል!

Weynafera Yohannes fb page

Related Articles


Post your comment

Sign in or sign up to post comments.

Comments

Be the first to comment